እኛ ማነን?

የ East Colfax ማህበረሰብ ጥምረት (EC3) ከነዋሪዎች፣ በአካባቢው ካሉ ነጋዴዎች፣ ለትርፍ ካልተቋቋሙ አካላት እና ጥምረቶች በተቋቋመ በማህበረሰብ የሚመራ፣ ብዘሀ ባህል፣ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚሰራ ተቋም ነው፡፡

ተልዕኳችን

የእኛ ተልዕኮ መፈናቀልን መከላከልና የማህበረሰባችንን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመወሰን የሚያስችል ድምር ሀይል መገንባት ነው፡፡

ራዕይ፡-

ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች እንዲሁም በአካባቢው የንግድ እንቅስቃሴው የተጠናከረ ብዝሀ ባህል ያለው ማህበረሰብ መሆን፡፡

የ East Colfax ማህበረሰብ ጥምረት:-

New Updates

Donate to The East Colfax Small Business Relief Fund

እኛ ምን እንስራ፡-

ፈጣን እገዛ፡-

መፈናቀሉን ተከትሎ አደጋ ላይ ላሉት ጎረቤቶቻችን እና ነጋዴዎች በቤት ውስጥ የድጋፍ ዘመቻ፣ በእኛ East Colfax ህጋዊ ክሊኒክ እና በእኛ East Colfax አነስተኛ ቢዝነስ ሪሊፍ ፈንድ በኩል ቀጥታ ድጋፍ አድርገናል፡፡

የቤት ችግርን መፍታት፡-

ማህበረሰቡ ለሚያልመው ራዕይ ስር የሰደደ ችግር የሚፈጥረውን ከቤት ጋር የተያያዘውን ችግር በቋሚነት እንፈታለን፡፡

የማህበረሰብ ግንባታ፡-

የአመራር ብቃትን ለማሳደግ፣ የማህበረሰቡን ግንኙነት ለማጠናከር እና በ East Colfax ያለውን ኩራት ከፍ ለማድረግ የተለያዩ መርሀግብሮችን እና ሁነቶችን አዘጋጅተናል፡፡

የአነስተኛ ንግድ ድጋፍ፡-

አነስተኛ ንግዶችን በንግድ ፍቃድ፣ እውቀና በመስጠት እና የመሬት ይዞታን በተመለከቱ እና በሌሎችም ጉዳዮች ድጋፍ እያደረግን ነው፡፡

የጥምረት ግንባታ፡-

ፍትሀዊ የቤት ፖሊሲን ለማሳደግ እና ማህበረሰቡን ያማከለ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል ሀይል በአካባቢው፣ በክልሉ እና በከተማው ደረጃ እየገነባን ነው፡፡

የፖሊሲ ድጋፍ፡-

የእኛ ማህበረሰብ በሁሉም ፖሊሲዎች ላይ ድምፃቸውን በማሰማት በጎረቤቶቻችን ላይ ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ አረጋግጠናል፡፡

ቁልፍ እሴቶች፡-

ማህበረሰብ መራሽ፡- EC3 ተፅዕኖው የደረሰባቸው ውሳኔ በማሳለፍ የሚያመጧቸው ውጤቶች ሁልግዜም ቢሆን የተሻሉ እንደሆኑ ያምናል፡፡

የቋንቋ ፍትሀዊነት፡- EC3 የማህበረሰባችንን ድምፅ ያከብራል፣ እና እያንዳንዱ ስለራሱ የመናገር መብት ያለው ስለመሆኑ፤ እንዲሁም በመረጡት ቋንቋ የመደመጥ መብት ያለው ስለመሆኑ ያምናል፡፡

ፍትሀዊነት፡- EC3 ሁላችንም ከአንድ ተመሳሳይ ቦታ አለመጀመራችንን የሚያሳውቁ ፖሊሲዎችን እና ተግባራቶች፣ ለየት ያሉ የህይወት ተሞክሮዎችን ለማስተዋወቅ የተዘጋጁ መሆናቸውን እና የእያንዳንዱ ማህበረሰብ ፍላጎት ስለመሆናቸው ቦታ ይሰጣል፡፡

ፈጠራ፡- EC3 ለመፈናቀል ጉልህና ዋና መፍትሄው በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉት ስር የሰደዱ አዳዲስ ሀሳቦች ስለመሆናቸው ያምናል፡፡

የሀይል ግንባታ፡- EC3 የምንሰራው ማንኛውም ነገር ለማህበረሰባችን ሀይል መገንባት ውስጥ አብሮ የሚካተት እንደሆነ ያምናል፡፡

መፍትሄ መራሽ መሆን፡- EC3 ችግሩን ከመጥቀስ በዘለለ መስራት እንዳለብን፤ ማለትም መፍትሄ ለማምጣት መጣር የግድ እንደሚያስፈልግ ያምናል፡፡

የእኛ ስኬቶች፡-

ጥቅምት 2019

EC3 የታተመ 2019 ፡፡

EC3 የተመሰረተው ኦክቶበር 2019 ሲሆን የ East Colfax Neighborhood (ECN) የወካይ ድምፅ መኖርን ለማጠናከር ከመጣ አስቸኳይ ፍላጎት የተነሳ የተመሰረተ ሲሆን በዚህም የልማት እቅዱ በማህበረሰባችን ላይ ለውጥ እንደሚያመጣና ከመፈናቀልም ማህበረሰቡን እንደሚጠብቀው የሚያረጋግጥ ነው፡፡

2020

የEC3 ስኬቶች በ 2020:
  • በ East Colfax የሚያጥጋሙ መፈናቀሎችን ለመከላል ተጨማሪ ከ65 በላይ የሆኑትን የዴንቨር ኢስት ኤሪኣ እቅድ ማጠናከሪያዎችን ማሸነፍ ችለናል፡፡
  • የቤቶች ድጋፍ ዘመቻ ያስጀመርን ሲሆን ከ $628,863 በላይ የሚሆን ገንዘብ ለኪራይ ድጋፍ አሰራጭተናል እንዲሁም ቀደም ሲል የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ያልነበሩ በተለይ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ያልሆኑ እንዲለቁ የተነገራቸው 36 ተከራዮች እንዳይለቁ ለማድረግ ችለናል፡፡
  • የአነስተኛ ንግድ ሥራ መታደጊያ ዘመቻ ነጻ የ East Colfax አነስተኛ ንግድ ሥራ መታደጊያ ፈንድ በተሳካ ሁኔታ ያቋቋመ ሲሆን $38,000 የሚሆን ገንዘብ በቀጥተኛ ግራንት አሰራጭተናል፡፡ በተጨማሪ በ East Colfax የሚገኙ 52 የአነስተኛ ንግድ ሥራ ባለቤቶች በአጠቃላይ $298,279 የሚሆን የኮቪድ-19 መጋደጊያ ግራንት እንዲያገኙ ማመልከት ላይ እገዛ አድርገንላቸዋል፡፡
  • 100 በመቶ የሆነ ቁርጠኝነት፡- ሁሉም የ EC3 ማህበረሰቦች ስብሰባዎች ከ2 እስከ 5 በሚደርሱ ቋንቋዎች የተተረጎሙ ሲሆን ይህም እኩል ተሳትፎን ለማረጋገጥ ረድቷል፡፡
Our Team

Board of Directors

Towanna Henderson

Board President

Nebiyu
Asfaw

Board Vice President

Rev. Laura Rossbert

Board Treasurer

Nathan Adams

Board Secretary

Jesus Gonzalez

Board Member

Htwe Htwe Aung

Board Member

Our Staff